Author Book

እውነት 💧 💧💧

Category: Religion
Language: Amharic
Edition: 1st Edition First Edition
Location: Addis Ababa
Business phone: +251911807200
Price: ETB 350.00
About the Author
ትዕግሥት ጎሳዬ መልካVerified Author

ወይዘሪት ትዕግሥት ጎሳዬ ኢትዮጵያዊት የሕግ ባለሙያና የአንድ ልጅ እናት ናቸው። ከብዙ ዉኃ አልባ መንፈሳዊ ደመናዎች በኋላ ባገኙት መንፈሳዊ ፍጹም ምልዓትና ባዩት የኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ ብርሃን እና ፍቅር እግዚአብሔር አምላካቸውን ያመሰግናሉ። ቅድስት ቤተክርስቲያንን፣ ቤተሰባቸውን፣ የቀድሞ ተማሪዎቻቸውን፣ የሥራ ባልደረቦቻቸውን፤ ወገኖቻቸውንና ውድ አገራቸውን ይወዳሉ። የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን (LL.B) በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ቤት አጠናቀዋል። በኖርዌይ ኦስሎ ዩኒቨርሲቲም ‘በዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ንድፈ ሐሳብና ተግባር’ (The Theory and Practice of Human Rights Law ) የማስተርስ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል። በአገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ተቋማት ከሐያ አምስት ዓመታት በላይ የዘለቀ የማስተማር፣ የአመራርና የተለያዩ የማህበራዊ ሳይንስ ዘርፎች ሞያዊ ልምዳቸውን በተለያዩ አገራት በቅንነት በማጋራት ላይ ይገኛሉ። በዚህም የመጀመሪያ መጽሐፋቸው ብዙዎች የቀና የሕይወትን መላና ጥበብ በጥቂቱም ቢሆን ያገኛሉ ብለው ተስፋ ያደርጋሉ።

From authors

Get it on Google Play