Browse authors
ይስማዕከ ወርቁ
Books, PDFs, audio, posts and resources on Waka Books
18 books
About
ይስማዕከ ወርቁ ኢትዮጵያዊ ወጣት ደራሲ ሲሆን ዴርቶጋዳ በተባለዉ መፅሀፉ በአንባቢዎቹ ዘንድ ታዋቂነትን አግኝቷል፡፡ ከዚህም ባሻገር ዴርቶጋዳ በአንድ አመት ብቻ 10 ጊዜ በመታተም እና በመጀመሪያ እትሙ ከ 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) በላይ ኮፒዎች በመሸጥ በኢትዮጵያ የመፅሀፍ ሽያጭ ታሪክ የመጀመሪያው መፅሀፍ ነው።
ይስማዕከ እስካሁን አስራ አምስት መፅሀፍትን ለህትመት አብቅቷል (የመጀመርያ መፅሀፉ)፣ የወንድ ምጥ የተሰኜው የግጥም መድብል ነው። የቀንድ አውጣ ኑሮ፣ ዴርቶጋዳ፣ ራማቶሓራ፣ ዣንቶዣራ ፣ ዮራቶራድ፣ ዮቶድ፣ ሜሎስ ፣ ተልሚድ ፣ ክቡር ድንጋይ፣ የኦጋዴን ድመቶች፣ ደህንነቱ፣ ተከርቼም እና ዛምራ የተሰኘ ልቦለድ ያበረከተልን ሲሆን የመጨረሻ ስራው ደግሞ በ አምሓራ ክልል ንፁሀን ህዝብ እና ሀገሪቱን እመራታለሁ በሚለው መንግስት መካከል ባለው አለመግባባት እንዲሁም በትግራይ ፣ በኦሮሚያ እና በአማራ መካከል የሚሞቱትን ሰዎች በግልፅ ቋንቋ "ግፉዓን"በሚል ኢ-ልቦለድ ድርሰት አቅርቦልናል። ከመጋቢት 2010 ዓ.ም ወዲህ በሀገሪቱ ላይ እየታየ ያለው ኢ-ፍትሐዊነትና የተበላሸ የመንግስት አስተዳደር የብዙ ንፁሀንን ህይወት እያሳጣን መሆኑን ይስማዕከ በ "ግፉዓን" ቁልጭ አድርጎ አሳይቶናል።
Works & related content
Browse marketplace listings, catalog titles, PDFs, audio, posts and public resources.






