Browse authors
ተክለ ጻድቅ መኩሪያ

ተክለ ጻድቅ መኩሪያ

Books, PDFs, audio, posts and resources on Waka Books

14 books
About ሽዋ ጠቅላይ ግዛት ካፈራቸው አንዱ ተክለ ጻድቅ መኩሪያ! (ከ1906_1992 ዓ. ም) ታላቅነት አይወረስም፣ ይቀዳጁታል እንጂ። ተክለ ጻድቅ መኩሪያ ከጐተራ ጸሐፊነትና የመዝገብ አለቃነት እስከ ሚኒስተርነት ፣ ከዚያም ዕውቅ ደራሲ እስከ መሆን የበቁት በመንፈስ ፅናትና ብርታት፣ በግል ጥረትና ቁርጠኝነት በመሆኑ ነው። ተክለ ጻድቅ መኩሪያ በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ውስጥ በምትገኘው አሳግርት ወረዳ አቆዳዳ ወይም ሣር አምባ መንደር መስከረም ፩(1) ቀን ፲፱፻፮(1906) ዓ.ም ተወልደው፣ ሐምሌ ፲፮(16) ቀን ፲፱፻፺፪ (1992) ዓ.ም ይችን ዓለም ሲለይዋት፣ ኢትዮጵያ ከብርቅየ ልጆቿ አንዱን አጣች። ተክለ ጻድቅን የመሰለ ታላቅ ዜጋ አረፈ እንጂ ሞተ አይባልም። ድርሳኖቻቸው ለዘለዓለም ሕያውነታቸውን ሲያወሱላቸው ሲያስመሰግኑአቸው ይኖራሉና። ‎ ‎ይህንን ውለታቸውን በመገንዘብ ነው ላዕከ ተክለማርያም ሐምሌ 20 ቀን 1992 ዓ.ም ለተክለፃዲቅ መኩሪያ ‎የሚከተለውን ቅኔ ያቀረቡት። ‎ ‎ተክለፃድቅ መኩሪያ ‎ያንድ ቤት ያስር ቤት የመቶ ቤት እያልን፣ ‎የታሪኩን ሂሳብ ገና እያሰላሰልን፣ ‎በሺ ቤት መቁጠሩን ሳንማርልዎ፣ ‎አቶ ተክለፃድቅ ምነው መሔድዎ ? ‎እንግሊዝ ፈረንሳይ ጣሊያኖች እረፉ፤ ሃሳብ አይግባችሁ፣ ‎አይመጣም እንግዲህ የኢትዮጵያን ታሪክ የሚጠይቃችሁ። ‎ያፄ ልብነ ድንግል የቦካን ተራራ፣ ‎ያፄ ፋሲል ጎንደር የመቅደላ ጎራ፣ ‎እንደ ተክለፃዲቅ ከሌለህ ወዳጅ፣ ‎ማን ይፅፍልሃል ተረስተህ ቅር እንጂ። ‎ተክለፃዲቅ መኩሪያ የበቀለብሺ፣ ‎ኩሪ አገሬ ቡልጋ ደብረ ፅላልሺ። ‎የተፈለፈለ የተሰራ ከአለት፣ ‎እንደ ላሊበላ እንደ አክሱም ሐውልት፣ ‎የታሪክ አምድ ነው ተክለፃዲቅ መኩሪያ፣ ‎መናኸሪያ እሚሆን መነሻ መድረሻ። ‎ታሪክ ይመላለስ እንደ ለመደው፣ ‎የማይመለሰው ተክለፃዲቅ ነው። ‎ከዚያ ከትልቁ ከሰማይ ቤት፣ ‎የምትፅፈውን ታሪክ ለመስማት፣ ‎ልሂድ ካንተ ጋራ አብሬ ልሙት፣ ‎ተክለፃዲቅ መኩሪያ የታሪክ አባት። ‎የተክለፃዲቅ ነፍስ ምን ቸግሯት ቦታ፣ ‎ቢሻት ከአብርሃም ጎን ከነ ይስሃቅ ተርታ፣ ቢሻት ከቴዎድሮስ ከዮሐንስ ጋራ፣ ‎ቢሻት ከምንልክ ከተፈሪ ጋራ፣ ‎ትኖራለች የትም እንደ ልቧ ሆና፣ ‎እየፃፈች ታሪክ በጽድቅ ብራና። ‎ታሪክ አልማርም ባፍንጫዬ ይውጣ፣ ‎ተክለፃድቅ መኩሪያ መምሕሬ ከታጣ። ‎ጥያቄ አትጠይቁኝ አታስቸግሩኝ፣ ‎ተክለፃድቅ መኩሪያ ማነው አትበሉኝ፣ ‎ጣይ ሞቆት ጣይ ሞቆት አገር ያወቀው፣ ‎ተረት ተረት ሳይሆን ታሪክ ፃፊ ነው። ተክለ ጻድቅ መኩሪያ በአማርኛ ጽፈው ለኢትዮጵያ ያበረከቷቸው 13 መፃህፍት! ፩: የኢትዮጵያ ታሪክ ኑብያ(ናፓታ-መርዊ) ፪:የኢትዮጵያ ታሪክ አክሱም-ዛጉዬ ፫:የኢትዮጵያ ታሪክ ከዐፄ ይኲኖ አምላክ- ዐፄ ልብነ ድንግል ፬ :የኢትዮጵያ ታሪክ ከዐፄ ልብነ ድንግል- ዐፄ ቴዎድሮስ ፭:የኢትዮጵያ ታሪክ ከዐፄ ቴዎድሮስ-ዐፄ ኃይለ ሥላሴ ፮: ከጣዖት አምልኮ ወደ ክርስትና ፯: የሰው ጠባይና አብሮ የመኖር ዘዴ ፰: ጥንታዊት ኢትዮጵያና ግብፅ ፱ : የግብፅ፣ የሳባና የኢትዮጵያ ፊደሎች (ማስታወሻ) ፲ : የግራኝ አህመድ ወረራ ፲፩: ዐፄ ቴዎድሮስና የኢትዮጵያ አንድነት ፲፪: ዐፄ ዮሐንስና የኢትዮጵያ አንድነት ፲፫: ዐፄ ምኒልክና የኢትዮጵያ አንድነት እንዲሁም የሕይወት ታሪካቸውንና በፈረንሳይኛ ቋንቋ ፭(5) መጻሕፍትን ጽፈዋል።

Works & related content

Browse marketplace listings, catalog titles, PDFs, audio, posts and public resources.

Books

Get it on Google Play