ህማማት ሄኖክ ኃይሌህማማት ሄኖክ ኃይሌ"ሕማማት" በዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ የተደረሰ፣ የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ሰሞነ ሕማማት፣ መከራና ስቅለት በጥልቀት የሚያስረዳ ታዋቂ መንፈሳዊ መጽሐፍ ነው። መጽሐፉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምእመናን ዘንድ እጅግ የሚወደድና በተለይም በዓቢይ ጾም ወቅት በስፋት የሚነበብ ነው።
የመጽሐፉ ዋና ዋና ይዘቶችመጽሐፉ በአጠቃላይ 6 ዋና ዋና ምዕራፎች እና 528 ገጾች ያሉት ሲሆን፣ የጌታን የመከራ ጉዞ ደረጃ በደረጃ ይተርካል፦
ምዕራፍ አንድ፦ የመጀመሪያው ቁስል
ምዕራፍ ሁለት፦ ሊቀ ካህናት በሊቃነ ካህናት ግቢ
ምዕራፍ ሦስት፦ የዓለማት ገዥ በይሁዳ ገዥ (በጲላጦስ) ፊት
ምዕራፍ አራት፦ የመከራ ጉዞ ወደ መከራ
ምዕራፍ አምስት፦ የመጨረሻዎቹ የጌታችን ትምህርቶች
ምዕራፍ ስድስት፦ የማይሞተው ሞተ
Please login to view seller contact details.