የኢትዮጵያ መንገድ ከፅልመት እስከ ንጋት

Negotiable

Price is negotiable
Condition: Like new
Category: Politics
Language: Amharic
Edition: 1st Edition
Publication Year: 2019
Location: Hawassa (turufat sefer)
Description

ይህ መጽሐፍ በኢትዮጵያ የሀገረ መንግስት ግንባታ ውስጥ ያሉትን ውስብስብ የፖለቲካኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ስነ-ልቦና ስብራቶች በመመርመር፣ “ከፅልመት” ወደ “ብርሃን”ለመሻገር አስቻይ መንገድ ይተነትናል። ጸሀፊው ሀገራዊ ቁስላችንን እያወሳ፣ ሀገር በቀልእሴቶቻችንን ከተራማጅ የፍትህ እሳቤዎች ጋር በማሰናሰል ትውልዱ ከተበዳይነት ትርክትወጥቶ የጋራ አሸናፊነትን፣ የህግ የበላይነትን፣ የሃሳብ ልዕልናን እና የሞራል ከፍታን በማስፈንከማንነታችን የተቀዳ አስተሳሰብ የብርሃን መንገዳችን ስንቅ ሊሆን እንደሚገባ ይመክራል።መፅሀፉ የነገው ብሩህ መንገዳችን የትላንትን ታሪክ እንደ ማነቆ ሳይሆን እንደ መማሪያየሚወስድ፣ ሀገሪቱ በጠንካራ ግለሰቦች ሳይሆን በማይናወጡ ተቋማት ላይ በመገንባት፣ እንዲሁምበጋራ መግባባትና በጥበብ የሚመራ ሊሆን እንደሚገባ አነቃቂ መከራከሪያዎችን ይሰነዝራል።በዚህም፣ የሀገሪቱን ስር የሰደዱ፣ ውስብስብ፣ መዋቅራዊና ግጭት አዘል ቋጠሮዎች ብሩህተስፋ (optimistic)፣ ግልፅ እና ቀላል በሆነ መልኩ (reductionist) የመፍትሔ መንገድማስቀመጡ መጽሐፉን ለአውንታዊ ግምገማ ብቻ ሳይሆን ለአሉታዊ ሙግት ይጋብዛል። ይህንየፀሃፊውን የብርሃን መንገድ ራዕይ ለመረዳት፣ ክርክሩን ለማዳበር፣ ለመሞገት ወይም ሚዛንላይ ለማስቀመጥ እያንዳንዱ አንባቢ መጽሐፉን ወደ ውስጥ ዘልቆ እንዲያነብ እና በጥልቀትእንዲፈትሽ እመክራለሁ።

Seller Information

Please login to view seller contact details.

Please login to view seller contact details.
Share
Please login to express interest in this book.
Get it on Google Play