ዝርዝር ግሶች በመዝሙረ ዳዊት

Negotiable

Price is negotiable
Condition: New
Category: Literature
Language: Amharic
Location: Addis Ababa (4 Kilo)
Description

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት መሠረት ከሀ ሉ ሒ ማ፣ ከአ ቡ ጊ ዳ፣ ከመልእክተ ዮሐንስና ከገበታ ሐዋርያት ቀጥሎ መዝሙረ ዳዊትን በግዕዝ፣ በውርድና በቁም ንባብ ተምሮ ማጠናቀቅ ዳዊት መድገም ይባላል፡፡ ታዲያ በዚኽ ዐይነት መልክ ተምረው ዳዊት ደግመዋል የሚባሉት ተማሪዎች ዳዊቱን በሦስቱ የንባብ ስልቶች ደግመው፣ ደጋግመው በማንበልበል ከማንበብ ባሻገር መልእክቱን በጥንቃቄ የመረዳት ውስንነት ዐልፎ ዐልፎ ይታይ ነበር። በአብነት ትምህርት ቤት ዳዊትን ባለ ማስተዋል የማንበብ ችግር አኹን ገና መፍቻ ቍልፍ ያገኘ ይመስለኛል፡፡ ይኽንም ማለት ያስቻለኝ ዕጩ ዶክተር ግዛቸው ደጀኑ በዋና አዘጋጅነት የሚመራው ዐሥራ ዐምስት አባላት የሚገኙበት የግዕዝ ሰዋስው አጠናቃሪ ቡድን፦ ዳዊትን አንብቦ በመረዳት ረገድ ዐዲስ የችግር መፍቻ ያመጣ መኾኑን መገንዘቤ ነው፡፡ ቡድኑ የተለያዩ ባሕርያት ያሏቸውን ግሶች በመምረጥ፣ የዋህና መለስተኛ መሠሪ ርባታዎችን በማርባት፣ የሚጠብቁትን ግሶችና የርባታ ኺደቶች በጥብቀት ምልክት በማሳየት፣ መረጃዎችን ከመዝሙረ ዳዊት ውስጥ ነቅሶ በማውጣትና በማቅረብ አመርቂ ሥራ አከናውኖ ዐይቻለኹ፤ የመጽሐፉን ረቂቅ ሙሉ በሙሉ አንብቤ ያገኘኹትን የንባብ ርካታ ተመርኵዤ ያለ ምንም መሠሠት ምስክርነቴን መስጠት ያስቻለኝም ይኼው የቡድኑ የሥራ ጥንካሬ ነው፡፡

ይኽ ዐይነቱ ቀና የሥራ አፈጻጸም በተለያዩ ሀገራት ተቀምጠው ወንጌላትን ከጻፉት ቅዱሳን ሐዋርያት የተቀደሰ ተግባር ጋራ የተመሳሰለ ነው፡፡ ቅዱሳኑ በጻፉትና ባስተማሩት የወንጌል ትምህርት ምክንያት «ድምፃቸው ወደ ምድር ዅሉ፣ ቃላቸውም እስከ ዓለም ዳርቻ ወጣ» (መዝ ፲፰/፲፱፣ ፬) ተብሎ ተነገረላቸው፡፡ ይኽ የግዕዝ ሰዋስው አጠናቀሪ ቡድንም በተለያየ የዓለም ክፍል እየኖረና በፈጣሪ መንፈስ እንደ ኤልያስ እየተመራ ግዕዝን በማሳወቅ ረገድ የላቀ ሚና እየተጫወተ ይገኛል፤ በባህላዊው ትምህርት ወቅት ይደረግ የነበረውን የማንበልበል የንባብ ኺደት ከግንዛቤ ጋራ ተያይዞ እንዲኼድና እያንዳንዱን የዳዊት ክፍል በማስተዋል እንዲነበብ በቂ ማሳያዎች ቀርበውበታል። እንዲኽም ሊኾን የቻለው በርባታው የተገኙትን ግሶች ከመዝሙረ ዳዊት መረጃዎችን ያካተተ እና ግሶች ዅሉ የርባታም፣ የፍቺም ኺደቶች የተከናወኑባቸው ስለኾኑ ነው፡፡ በዚኽ ምክንያት ነው አኹን ገና ዳዊትን ያለ መገንዘብ ችግር መፍቻ ቍልፍ አገኘ የተባለው። ስለዚኽም ይኽን ዐይነቱን ዳዊት ድገሙ እየተባለ በሚመከርበት በአኹኑ ጊዜ እንደዚኽ ያለውን ወቅታዊ መጽሐፍ አግኝቶ ማንበብ እጅጉን መታደል ነው እላለኹ፡፡

ዘላለም መሠረት ተገኘ (ዶ/ር)

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የግዕዝ ቋንቋና የጥንታዊ ሥነ ጽሑፍ መምህር

* * ***

ግእዝ ለዘመናት የኢትዮጵያን መንፈሳዊ፣ ምሁራዊና ባህላዊ ቅርስ የጠበቀ የጥንት የጽሑፍ ቋንቋ ነው፡፡ ይኽን ክቡር ቅርስ በጥናትና በትምህርት ለማስቀጠል እየተጉ ካሉ ምሁራን መካከል ዕጩ ዶ/ር ግዛቸው ደጀኑ አንዱ ነው:: በግእዝ ቋንቋና ሥነ ጽሑፍ ያለውን ዕውቀት በማካፈል ብዙ ተማሪዎችን አፍርቶ ለግእዝ ጥናት ጕልሕ አስተዋፅኦ አበርክቷል፤ እያበረከተም ይገኛል። ይኽ መጽሐፍም የዚያ ትጋት ማሳያ ነው። «ዝርዝር ግሶች በመዝሙረ ዳዊት» በተሰኘው በዚኽ ሥራ፣ ዕጩ ዶ/ር ግዛቸው ከተማሪዎቹ ጋራ በመተባበር የግእዝ ግስ ዝርዝር ርባታን መዝሙረ ዳዊትን መሠረት በማድረግ፣ በግልጽና በሥርዐት በመተንተን አዘጋጅቷል፡፡ በመኾኑም መጽሐፉ ለምሁራን፣ ለሥነ ልሳን ተመራማሪዎች፣ ለጉባኤ ቤት መምህራንና ተማሪዎች እጅግ አስፈላጊ እና ለግእዝ ቋንቋ ጥናትና ምርምር የማይተካ የማጣቀሻ ምንጭ እንደሚኾን አምናለኹ፡፡

አንዱዓለም ኤርምያስ (ዶ/ር)
በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ የጥንታውያን መዛግብት ጥናት መምህር

Marketplace

Seller Information

Please login to view seller contact details.

Please login to view seller contact details.
Share
Please login to express interest in this book.
Get it on Google Play