About This Event
ምስጢረኛው ባለቅኔ
ሎሬት ፀጋዬ ገብረ መድህን፡ ጥበብ፣ ማንነትና ኢትዮጵያዊነት
✍️ «እኔ ለእኔ ኖሬ አላውቅም…»
ይህ የሎሬት ፀጋዬ ገብረ መድህን የሕይወት ፍልስፍና የሚገልጽ የጥበብ አሻራ ነው። ለሕዝብ፣ ለአገርና ለሰው ልጅ በግጥሙና በተውኔቶቹ የተናገረው ሎሬት፣ ከዘመኑ አልፎ ዛሬም የምንመረምራቸውን ጥያቄዎች ትቶልናል።
በቅኔው ውስጥ የተሸሸጉት ምስጢሮች ምንድን ናቸው? ስለ ማንነት፣ ስለ ኢትዮጵያዊነት፣ ስለ አፍሪካዊነትና ስለ ሰው ልጆች አንድነት ያለው አስተሳሰብስ ምን ይነግረናል?
ሆሄ የሥነ ጽሑፍ ሽልማት በዚህ ሳምንት መጨረሻ በሚያዘጋጀው የመጻሕፍት ውይይት፣ «ምስጢረኛው ባለቅኔ» በተሰኘው መጽሐፍ አማካይነት የሎሬቱን የጥበብ ዓለም በጥልቀት እንቃኛለን።
📖 በውይይታችን የምንመረምራቸው ጉዳዮች፦
🔹 የሎሬት ፀጋዬ የሥነ ጽሑፍ ውርስና የጥበብ ፍልስፍና፤
🔹 በግጥሞቹና በተውኔቶቹ ውስጥ የተንጸባረቁ የማንነት፣ የኢትዮጵያዊነትና የአፍሪካዊነት ሐሳቦች፤
🔹 በቅኔና በምሳሌ የተሸፈኑ መልዕክቶችን መተርጎምና የዘመናችንን ጥያቄዎች ከሥራዎቹ አንጻር መመልከት፤
🔹 የሎሬቱ ሥራዎች በማኅበራዊ ለውጥ፣ በፍትሕና በሰላም ግንባታ ያላቸው ሚና።
🎙️ የውይይቱ ተሳታፊዎች
አወያይ፦ ዳግማዊ አመለወርቅ
አቅራቢዎች፦
▪️ ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ
▪️ ለዓለም ብርሃኑ
▪️ ሚካኤል ሽፈራው
በዚህ ውይይት ከመጽሐፉ ይዘት ባሻገር፣ የሎሬቱን የጥበብ አሻራ፣ የሐሳብ ጥልቀትና በትውልድ ላይ ያሳረፈውን ተጽዕኖ በተለያዩ እይታዎች እንመለከታለን።
📌 ማስታወቂያ፦ የሎሬት ፀጋዬ ገብረ መድህንን ተውኔቶች በመተወንና በማዘጋጀት ያካበተውን ልምድ ሊያካፍለን የነበረው ተስፋዬ ሲማ፣ በሥራ ምክንያት ወደ ውጭ አገር በመሄዱ በዚህ ውይይት መሳተፍ አልቻለም።
━━━━━━━━━━━━━━
📅 ቀን፦ ጥቅምት 14 ቀን 2019 ዓ.ም.
📍 ቦታ፦ ወመዘክር
🕓 ሰዓት፦ ከጥዋቱ 4፡00 ጀምሮ
━━━━━━━━━━━━━━
📚 ሥነ ጽሑፍ ያገናኘናል፤ ውይይት ያቀራርበናል፤ እውቀት ያነቃናል!
በሆሄ ምዕራፍ እንገናኝ።
የመጻሕፍት ወዳጆች፣ ገጣሚያን፣ ደራሲያን፣ ተመራማሪዎችና የሐሳብ ውይይት ወዳጆች ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!