All Reviews
Book cover
ያለተቀበሩ ስሞች ቅጽ ፩

by አባትነህ ካሤ አሸናፊ

5.0 avg · 1 review
T
Tsegaw Mamo
2 reviews · 0 followers · August 8, 2026
5/5

"ያልተቀበሩ ስሞች" ቅጽ ፩

የመቃብር ላይ ጽሑፎችን ማንበብ እጅግ ያዝናናኝ ነበር ... እናም አንድ ወቅት ሰማይ ምድሩ የሚያሸረግድላቸው ታላላቅ የየዘርፋ ጀግኖችን መካነ መቃብር ስጎበኝ ህልቆ መሳፍርት ሃሳቦችና መደነቆች መላ አካላቴን ይመላዋል ።የሕይዎትን ጣፋጭ ትርጉም አጣጥማለሁ...የወጣቶቹን ቁንጅና እና አሟሟት እያየሁ በጥልቅ እመሰጣለሁ... የቅድስት ሥላሴን መካነ መቃብር ስጎበኝ የመካነ መቃብሩ ጀግኖች በመጽሐፍ መጻፍ እንዳለበት ይሰማኝ ነበር። ~~~~~~~~ እናም ያንን ምኞቴን ያሳካ ❝ያልተቀበሩ ስሞች ቅጽ ፩❞ በሚል ርእስ በቅድስት ሥላሴ ካቴደራል አጽማቸው ያረፉ እጅግ የምናከብራቸውን ሀገር የሰሩ የጀግኖች አባት አርበኞችን ፣ ፓትሪያሪኮችን ፣የሀገር መሪዎችን ፣ አስተዳዳሪዎችን ፣ዲፕሎማቶችን ፣ ታላላቅ ደራሲያንን፣ የኪነ ጥበብ ሰዎችን ፣ድምጻውያንን ፣ ጋዜጠኞችን ፣ የማስታወቂያ ባለሙያዎችን፣ ጀግኖች አትሌቶችን፣ ታላላቅ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንትን እና የተለያዩ ተጽእኖ ፈጣሪ ሰዎችን ታሪካቸውን በጥናት ተሰንዶ በመጽሐፍ መቅረቡ እጅግ የሚያስመሰግን ሥራ ነው ።የመጽሐፉ ደራሲ "አባትነህ ካሤ" ምሥጋና ይገባዋል። እናመሠግናለን።
Comments (0)
Login to leave a comment.
T
Tsegaw Mamo
2 reviews · 0 followers
View All Reviews
Have you read this book?

Share your own review and help the community.

Write a Review
Get it on Google Play