ሥራ የሚፈለግ ሳይሆን የሚፈጠር ነው
ገብረስላሴ በአምላከ · ETB 200.00
Open
ይህን መጽሐፍ በእጅህ ያደረግኸው ለንባብ ብቻ ከሆነ፤ የመጽሐፉን ዋና ዓላማ ገና አልተረዳኸውም።
ይህ መጽሐፍ ገጽ እየገለበጥክ ብቻ እንድታልፍ የተጻፈ አይደለም፤ ይልቁንም ሕይወትህን እንድትቀይር የተዘጋጀ ነው።
ለረጅም ጊዜ ሥራ እየጠበቅክ ከሆነ፤ ምናልባት ችግርህ ዕድል ማጣት ሳይሆን ዕድልን የማየት አቅጣጫህና አመለካከትህ ሊሆን ይችላል።
አንተ ችግር ያየህበት ቦታ ላይ ሌላው ሰው ትልቅ ዕድል ሊያይበት ይችላል።
መልካም ሀሳብ ብቻ ይዘህ ከተቀመጥክ፤ ሀሳብህ ብቻውን ሕይወትህን አይለውጠውም፤ ወደ ተግባር ስታወርደው ግን ለውጥህ መጀመሪያ ይሆናል።
ይህ መጽሐፍ እንድታስብ ብቻ አይጋብዝህም፤ እንድትሠራና እንድትራመድም ይገፋፋሃል።
ከ«ሥራ እፈልጋለሁ» አስተሳሰብ ወደ «ሥራ እፈጥራለሁ» አቋም እንድትሸጋገር ያደርግሃል።
ከችግር ወደ ዕድል፤ ከሀሳብ ወደ ተግባር፤ ከተግባር ደግሞ ወደ ጨበጥ ውጤት የሚወስድህን ብሩህ መንገድ ታያለህ።
የምታነበውን እውነት በሕይወትህ ላይ ስትተገብረው፤ የመጽሐፉ ትክክለኛ ዋጋ ያኔ ይገለጥልሃል።
ስለዚህ እባክህ ይህን መጽሐፍ እንደ ልብወለድ ታሪክ አታንብበው፤ ይልቁንም እንደ ተግባራዊ መመሪያ ተጠቀምበት።
ይህን መጽሐፍ ለመተግበር የቆረጥክ ከሆነ ብቻ አንብበው!
ምክንያቱም መጽሐፉ በመጨረሻ የሚጠይቅህ አንድ ወሳኝ ጥያቄ ብቻ ነው።
«ካነበብከው በኋላ ምን ታደርጋለህ/ሽ?»
ከዚህ በኋላ ያለው ምዕራፍ የመጽሐፉ አይደለም፤ የእንተ / የእንቺ የሕይወት ምዕራፍ ነው።
Please login to view seller contact details.