«ደራሲው» የተሰኘው ልብወለድ መጽሐፍ በኢትዮጵያ ሥነ-ጽሑፍ ውስጥ ስለደራሲያን ሕይወት ፣ ስለጥበብ ትርጉም እና ስለ ማህበራዊ ግዴታዎች በጥልቀት የሚተነትን ድንቅ ስራ ነው።
በአሉ ግርማ ለዚህ መጽሐፍ እንደ ዋና መረጃ ምንጭ የተጠቀመው በጋዜጠኝነትና በደራሲነት ሙያው የስራ አጋሩ ሆኖ ያሳለፈውን የስብሃት ገብረእግዚአብሄርን የግል ተሞክሮ ሲሆን በመጽሐፉ ውስጥ የሚነሱት ሐሳቦች ስብሃት በወቅቱ ካጋጠሙት እውነታዎች የተወሰዱ ናቸው። በአሉ በመፅሐፉ «ደራሲነት» ዝና ወይም ገንዘብ ማግኛ ብቻ ሳይሆን ከባድ ማህበራዊ ኃላፊነት መሆኑን ለማሳየት ይሞክራል።መጽሐፉ አንድ ደራሲ ከራሱ ህሊና ፣ ከኪነ-ጥበብ ህግጋትና ከማህበረሰቡ ፍላጎት ጋር የሚያጋጥመውን ፍጥጫ በመመረምር ለአንባቢያን ትልቅ ግንዛቤ ይሰጣል።
Please login to view seller contact details.