<<አጼ ላሊበላ ግን የዓባይን ውኃ ከየመንገዱ አውጥቶ ወደ በረሃ በመስደድ እጅግ የሚያስቸግርና የማይቻል መሆኑን አውቆ ለዓባይ ውኃ ኃይልና ብርታት የሚሰጡትን በዝናብ ጊዜ ብዙ ጉርፎ እየያዙ ወደ ዓባይ የሚገቡትን ከየተራራው የሚወርዱትን ወንዞች ሁሉ ወደ ዓባይ እንዳይገቡ እያቋረጠ ወደ ሌላ ስፍራ ለመስደድ ጀመረ። በዚህም ሁሉ ምክንያት የላሊበላ ስሙ በሙሉ ኢትዮጵያ በውጭም አገረ ሁሉ የታወቀ ሆነ። በመሬትም ውስጥ የታነጹትን አብያተ ክርስቲያናት ለማየት የኢትዮጵያ ሕዝብ ከየአውራጃው እየተሰበሰቡ በያመቱ እየሄዱ እንደ ኢየሩሳሌም አክብረው ይሳለሙታል። ስፍራውም ገዳመ ሮሐ ወይም ደብረ ሮሐ ተብሏል።...>>
Please login to view seller contact details.