ሌኒን (ታላቁ አብዮተኛ )
በታላቁ ቮልጋ ወንዝ ዳርቻ በ1870 ከድሃ ቤተሰብ ተወለደ ። ገና በልጅነቱ የታላላቆቹን የሩሲያ ደራሲያን መጽሕፍት ጠንቅቆ አነበበ ። ብዙውን ጊዜ አያሌ መጻህፍትን በማለዳው ተሸክሞ ወደ ጫካ እየሄደ በማንበብ ያሳለፈ ጀግና ነው ።
ሌኒን መላዋ ሩሲያን ያንቀጠቀጠ የድሃ ልጅ ነው ።በማርክስና በኤንግልስ ጽንሰ ሃሳብ መሰረቱን አድርጎ የሩሲያን ከተሞች ወደ ጥናት ክበብ ቀየራቸው ፤ አብዮቱን በጠንካራ መልእክቶቹ አቀጣጠለው ፤ በተደጋጋሚ ይታሰር ነበር ይሁንና በአስቸጋሪ እስር ቤት ውስጥ ሆኖ በመጽሐፍትና በጋዜጣ ጽሁፎች መካከል ባለ ክፍት ቦታ በወተት እየጻፈ ፣ ለወተት መያዣ ከዳቦ ብልቃት እየሰራ ለውጡን በተሳካ ሁኔታ መርቶታል ።
ትክክለኛ ስሙ ቭላድሚር ኢልይች ሲሆን "ሌሊን" የሚለውን ስሙን ከታሰረባት የሳይቬሪያ ወንዝ "ብሌና" የተወሰደ እንደሆነ ብዙዎች ይስማማሉ። ሌሊን እጅግ ቅን አሳቢ ፣ ሩህሩህ ፣ሰዎችን ሁሉ አክባሪ ፣ጨዋ እንደሆነ ከራሽያ እስከ ህንድ ድረስ ይመሰክሩለታል ። ይሁንና በቀዩ ጦሩ ሚሊዮኖች እንደ ቅጠል የረገፉት በእርሱ ምክንያት እንደሆነ ስናስብ ሩህሩህነቱ ጥያቄ ውስጥ ይከተናል።
ሌኒን ከካዛን ዩኒቨርስቲ በህግ የተመረቀ ፣ እጅግ ሰዓት አክባሪ ፣ ኢስካራ እና ብራቭዳ በተባሉት ተዋቂ ጋዜጦቹ ምድርን ያንቀጠቀጠ ድንቅ የአብዮት ጸሐፊ ነው ። ሌኒን በወቅቱ በመላ ራሽያ ተወዳጅ ነበር ። ሌኒን ለዘላለም ይኑር የሚል መፈክር በየ እለቱ ይስተጋባ ነበር ።
ሌኒን የራስን እድል በራስ መወሰን ፣ ትምክህተኞችንና አድርባዮችን መታገል ፣ የወዛደር አምባ ገነንነት መፍጠር ፣ ሰራተኛውንና ገበሬውን ማሳደግ በሚል መሪ ሀረጎች የህብረት ስራ ማህበርን አደራጀ ፣መሃይምነትን ለማስቀረት ሰራ ፣ ታላላቅ ኢንደስትሪዎችን አቋቋመ ፣የባህል አብዮትን አፋፋመ ፣ ነጻ የህዝብ ህክምናንናና ብዙ ነገሮችን በአብዮት መልክ በሩሲያ ምድር የሰራ አሞተ መራራ መሪ ነው ።
ታላቋን ራሽያ ከመሰረቷ ነቀነቃት ፣ የዘመናት ጀግኖቿን ናቀ ፣የራሽያ የሆኑትን ሁሉ አጣጣለ ፣ ራሽያን በተቃርኖ ውስጥ ሊመራት የመሰረት ድንጋይ ጣለ ። ራሽያን የኋላ ኋላ ዋጋ አስከፈላት።የእኛም አገር የ60ዎቹ ተማሪዎች ወጉ ይድረሰን ብለው የሌኒንና የጆሴፍ እስታሊንን በቀጥታ በመገልበጥ በታገል ፣ በዲሞክራሲያ ፣ በሰፊው ህዝብ ጋዜጦች በመጻፍ እራሳቸውን እንደ አዋቂ ቆጠሩ... ይኸ ዓለም ላይ ሞቶ የተቀበረ አስተሳሰብ ካልተገበርን ብለው ከፊሎቹ ጫካ ገቡ ከፊሎቹ በከተማ እርስ በርስ ተጋደሉ... ዛሬም እኛን ኢትዮጵያኖችን እየፈተነን ይገኛል ።
ሌኒን ብዙ ጊዜ ታስሮአል ፣ ከአገር ውጭ በስደት ኖሮአል ፣ የሞት ፍርድም ተፈርዶበታል ፣ ሁለት ጊዜም ከሞት አደጋም ተርፏል... ይሁንና ያሰበውን ዓለማ ከ15 ዓመት መራራ ትግል በኋላ በድል አሳክቷል ። በመጨረሻም በ1924 በአንጎል ደም መፍሰስ ታሞ አረፈ ።
የሌኒን ትግል ከራሽያ አልፎ ዓለምን አነቃንቆ ያለፈ አስደናቂ ክስተት ነው ። አሳዛኙ ነገር በዓለም ላይ በተግባር ተፈትሾ እልቂትንና ውድቀትን ያስተናገደ ርዕዮተ ዓለም በእኛ አገር እንደ አዲስ መቀንቀኑና እስካሁኗ ሰዓት አገራችንን እግር ቶርች ያሰራት የሌኒን እሳቤ መሆኑን አለመረዳታችን ነው ።
ይህንንና ሌሎች መጻሕፍት ካነበባችሁ በኋላ የእኛ አገር ፖለቲካ ያረጀ መሆኑን ትረዳላቸሁ ።
ምንጭ
የሌኒን አጭር የህይወት ታሪክ... በ1980 ዓ.ም በኘሮግሬስ የመጻሕፍት ማዘጋጃ ቤት የተተረጎመ.
Please login to view seller contact details.