ይህን መጽሐፍ የሚያብቡ አፍቀርያነ መጻሕፍት፡ አንዲት፡ ቅድስት፡ ኵላዊትና ሐዋርያዊት የሆነችው የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን በየዘመናቱ የተነሡባትን ኑፋቄያት ለመመከት ያደረገችውን ታላቅ ተጋድሎ እየተደመሙ ይማሩብታል፡፡ ኑፋቂያትን መቃወም ብቻ ሳይሆን፡ የእምነት አርበኞች የሆኑት የቤተ ክርስቲያን ታላላቅ አባቶች ቅዱሱን መጽሐፍ መሠረት በማድረግ አርቶዶክሳዊውን አስተምህሮ በማያሻማ መልኩ የገለጹበት ሂደትም በዚህ መጽሐፍ በዝርዝር ስለተዳሰስ፡ መጽሐፉ የእናት ቤተ ክርስቲያናቸውን ትምህርተ ሃይማኖት በተሻለ መልኩ ለማወቅ ለሚፈልጉ ሰዎች ጠቀሜታው እጅግ ከፍ ያለ ነው::
Please login to view seller contact details.