" የጎጃም ገዥ ራስ ኃይሉ ከአያሌ ኮከብ ቆጣሪዎችና ጠንቋዮች ጋር ወዳጅ ናቸውና በአራሽዎችና በጠንቋይዎች ማሃከል በሚባለው ነገር ለመግባት መጀመሪያ አልወደዱም። የሚያስደንቀው እንግዳ ወሬ በሃገር ሲወራ ዝም አሉ።
ዝናብና በረዶ ይቅርና ፥ ብሩህ የሆነው ደመና እንኳ ከሃገራችን ሰማይ በሚጠፋበት ጊዜ ከጥቅምት እኩሌታ አንስቶ እስከ ጥር መግቢያ አጠገብ ድረስ ብርቱ ዝናብና በረዶ በየቀኑ ጣለ። አፍርተው ዛላቸው ተሸክሞ የነበሩ አዝመራዎች ቀጠቀጣቸውና ጎርፍ ደግሞ መልሶ ከወጡበት መቃብር አገባቸው። የገበሬዎች እጅ በአዝመራቸው ውስጥ ነዶ ለማሰር የቀን ሕልም ሆነባቸው፤ አራሽ የደከመበት አዝመራ ሁሉ ከንቱ ሆነ።
አገሪቱ በሙሉ ታወከች፤ ታላቅ ሁከት ሊያደርግ ሕዝብ ደግሞ ተንቀሳቀሰ።
አገሪቱ በሙሉ ታወከች፤ ታላቅ ሁከት ሊያደርግ ሕዝብ ደሞ ተንቀሳቀሰ።
ራስ ኃይሉ በሁለቱ መካከል ለመቆም ከቶ አይችልምና ጠንቋይና ኮከብ ቆጠሪ የተባሉ ሁሉ እንዲያዝ ትዕዛዝ ተሰጠ። ፈረሰኛ ወታደር ኮከብ ቆጣሪዎችና ጠንቋዮችን ሁሉ እንደ ሌባ ከየቤታቸው እንደ ግልገል ድመት እያነቁ ለፍርድ ወሰዳቸው። ሰማይን ለመክፈትና ለመዝጋት በጥበባቸው ሥልጣን እንዳላቸው ያወጁ ሽማግሌዎች ከታዘዘው ከምድራዊ ፈረሶች ፊት ሸሽተው እንደቀበሮ ወደ ጫካ ውስጥ ተሸሸጉ። ነገር ግን የቀበሮን ዱካ ገበሬ ይወቃዋልና ከተሸሸጉበት ጫካ ውስጥ ሳይቀር እየጎተቱ ለፍርድ ቀረቡ።
ምንም እንኳ ያን የነበረኝን የኮከብ መቁጠሪያና የጥንቆላ መፅሐፍቶችን አባቴ ቢያቃጥላቸውም በፈቃዴ ወደ ጨካኙ ፈራጅ ሄድኩኝ። በገጠመኝ የሁሉ አቤቱታ የቀላጤ ደብዳቤ ፀሃፊ ሆንኩኝ።
ለሁሉም አርባ አርባ በበሬ ጅራፍ እንደ በሬ ሲገረፍ ከዚህ ሌላ ሶስት መቶ ብርና ከዓመት እስከ ሁለት ዓመት ድረስ እንዲታሰሩ ተፈረደባቸው።
(ሕይወቴ ፣ ተመስገን ገብሬ)
Please login to view seller contact details.