"ትንሽ ብታስብበት መብላት እጅግ የሚያሳፍር ተግባር ነው።ቄራ ውረድና አንድ ሰአት ያህል አስተውል ። በሬውን አንገቱን ገዝግዘው ሲያርዱት ቆዳውን ሲገፉት ብልቱን ሲለያዩት ፈርሱን ሲጎለጉሉት ተመልከት። ሆቴል ግባና አይንህን ጨፍነህ ህዝቡ ሲያኝክ አጥንት ሲቆረጣጥም ስማ ።
አክ! ምን አይነት መጨማለቅ ይሄ ሁሉ ያችን የግማት ስልቻ ለመሙላት ቀበቶህን ባጠበቅክ ቁጥር ፈርስ እንደሚጨፈልቅ አስበህበታል?
ልክ የጎለጎሉትን የበሬውን ፈርስ የሚመስል ።
ለመሆኑ በሬውን ሲያርዱት በስመ አብ ብለው ሲጀምሩ አይገርምህም? እኔ በበኩሌ ይህን በስመ አብ ብሎ ማረድ የጀመረው ቀልደኛ ቄስ ነው እላለሁ ቀልድ ካልሆነ እንዴት የአብን ፍጡር በአብ ስም ትገድለዋለህ?"
Please login to view seller contact details.