ዶክተር በድሪ ሙኒር ዩሱፍ በአዳማ ከተማ ተወልዶ አድጓል። የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በአዳማ ፋና፣ በቅዱሥ ዮሴፍ እና በገላውዴዎስ ትምህርት ቤቶች ተከታትሏል። የጤና ሙያ ጉዞውን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጎንደር ሕክምና ኮሌጅ በሕክምና ዶክትሬት በመመረት የጀመረ ሲሆን በዚያው ሆስፒታልም በሐኪምነት አገልግሏል።
የከፍተኛ ትምህርቱንም በመቀጠል በጀርመን በላይፕዚግ ዩኒቨርሲቲ በቆዳና አባለዘር በሽታዎች ዘርፍ የድህረ ምረቃ ስልጠናውን አጠናቋል። ከዚያም በናሚቢያ እና በደቡብ አፍሪካ ለጥቂት ጊዜ ከሠራ በኋላ በአሜሪካ አትላንታ ከተማ በውስጥ ደዌ ትምህርት ስፔሻላይዝ አድርጓል። ከዚህ ጎን ለጎን ከማሳቹሴትስ ዩኒቨርሲቲ በቢዝነስ አስተዳደር የማስተርስ ዲግሪውን አግኝቷል።
በአሁኑ ወቅት በጆርጂያ ግዛት በተለያዩ የጤና ተቋማት ውስጥ፤ በውስጥ ደዊ እና በከፍተኛ የአመራር ዘርፍ በማገልገል ላይ ይገኛል። ዶክተር በድሪ ባለትዳርእና የሁለት ልጆች አባት ሲሆን በአሁኑ ወቅት ነዋሪነቱ በአትላንታ ከተማ ነው፡፡
Please login to view seller contact details.